የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ቀዳማዊ መሠረታዊ የሠራተኛ ማህበር ለተማሪዎች የመማሪያ ደብተር ድጋፍ አደረገ፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ቀዳማዊ መሠረታዊ የሠራተኛ ማህበር መስከረም 13 ቀን 2018 ዓ.ም ለተማሪዎች የሚሆን 1,000,000 (አንድ ሚሊዮን ብር) የሚገመት የመማሪያ ደብተር ለአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ አስረከበ፡፡
በርክክብ ስነ-ስርዓቱ ላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ቀዳማዊ መሠረታዊ የሠራተኛ ማህበር አመራሮች፣ የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ አመራሮች እንዲሁም ተማሪዎችና መምህራኖች ተገኝተዋል፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ቀዳማዊ መሠረታዊ የሠራተኛ ማህበር ፕሬዝደንት አቶ መገርሳ አስፋዉ ባደረጉት ንግግር ማህበሩ የወከለዉን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ሠራተኞች መብትና ጥቅም ከማስከበር ባለፈ በተለያዩ የማኅበራዊ ኃላፊነት ስራዎች ላይ በንቃት የሚሳተፍ ሲሆን ይህ የመማሪያ ደብተር ልገሳም የዚሁ ጥረት አካል መሆኑን ገልጸዋል። ማህበሩ የነገ ሀገር ተረካቢ ለሆኑ ዜጎች ድጋፍ በማድረጉ ከፍተኛ ኩራት እንደሚሰማው ጠቁመው ፤ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ጋር በመሆን የትምህርት ስራው ውጤታማ እንዲሆን የበኩሉን አስተዋጽኦ እንደሚያደርግ ገልጸዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ቀዳማዊ መሠረታዊ የሠራተኛ ማህበር የትምህርት ስራ የሁሉንም ባለድርሻ ተሳትፎ የሚፈልግ ተግባር መሆኑን በመገንዘብ ለተማሪዎች የመማሪያ ደብተር ድጋፍ በማድረጉ በራሳቸው እና በተማሪዎች ስም ምስጋና በማቅረብና ልገሳው ለተማሪዎች ትምህርት ከፍተኛ ትርጉም ያለው አስተዋፅኦ እንደሚያበረክት ገልጸው ማህበሩ ላደረገው ጠቃሚና ከፍተኛ ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ይህ የተደረገዉ ድጋፍ ማህበሩ ለማኅበራዊ ኃላፊነት ስራዎች ያለውን ቁርጠኝነት በከፍተኛ ሁኔታ የሚያመላክት ሲሆን ወደፊትም ከዚህ በበለጠ ሁኔታ በተለያዩ ማኅበራዊ ኃላፊነት ስራዎች ላይ ጠንክሮ በመስራት የበኩሉን አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ለመግለጽ እንወዳለን፡፡
Building a Strong Future Together!!
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ቀዳማዊ መሠረታዊ የሠራተኛ ማህበር!
Ethiopian Airlines Group Primary Basic Trade Union!

